View Lyrics: ኢየሱስ ኢየሱስ ወዳጄ Modal close icon

Viewing lyrics for ኢየሱስ ኢየሱስ ወዳጄ by Eyerusalem Negiya.

ኢየሱስ ኢየሱስ ወዳጄ
ኢየሱስ ኢየሱስ መድሃኔቴ
ከአፌ አላወርድም ይህን ስምክን
አላርፍም አልረካም እስካገኝህ/2

ውሃ በማጣት እንደደረቀ መሬት
አግኝታ እስክትረካ ነፍሴ እያት ስትዋትት
ኋይልና ሞገስህ በሞላ መቅደስ
ፍቀድልኝና ልየው ያን ፊትህን
እንጨትና ውሃ በሌለበት ቦታ
እኔ ግን ሄዳለሁ ውድዬን ፍለጋ
አንድ ጊዜ ብቻ አስበኝ መድህኔ
ጠግቤ ኖራለሁ በሕይወት ዘመኔ
አንድ ጊዜ ብቻ አስበኝ ረድኤቴ
ፍቅርህ መድሃኔት ነው ፈውስ ለሕይወቴ

ኢየሱስ ኢየሱስ ወዳጄ
ኢየሱስ ኢየሱስመድሃኔቴ
ከአፌ አላወርድም ይህን ስምክን
አላርፍም አልረካም እስካገኝህ/2

የተመኘሁትን ያሰብኩትን ይዤ
ገና አልረካሁኝም አለሁኝ ተክዤ
ጎተራዬ አልሞላም ፍላጎቴ አልቆመ
የውስጠቴን ረሃብ ይህ አላጠገበ
ወዳንተ እጠጋለሁ ሙጥኝ እልሃለሁ
ያገኘሁህ ለታ እንዴት እሆናለሁ
ሰው መልካም ምግብን በልቶ እንዲጠግብ
ነፍሴ ትጠግባለች በክብርህ በግርማህ
ሰው መልካም ምግብን በልቶ እንዲጠግብ
ነፍሴ ትጠግባለችጌታዋን ስታስብ
ኢየሱስ የሕይወቴ ፍስሀ
ኢየሱስ ብኖር በበረሃ
ኢየሱስ የሕይወቴየህይወቴብርሃን
ኢየሱስ የሕይወቴ ባልፍም በጨለማ
አንድ ጊዜ ብቻ አስበኝ ረድኤቴ
ፍቅርህ መድሃኒት ነው ፈውስ ለህይወቴ
አንድ ጊዜ ብቻ አስበኝ መድህኔ
ጠግቤ ኖራለሁ በሕይወት ዘመኔ

በመጠበቂያዬ በማማዬ ሆኜ
እጠብቅሃለሁ እንዳይህ አምኜ
ዝለቴ ድካሜ ይወገድ ሀፍረቴ
በሰፈሬ እንድታልፍ እንድትገባ ቤቴ
ባላሰብኩት ሰዓት ባልጠበኩት ቦታ
በጊዜ ሰሌዳ ባንታ አቆጣጠር
የጠበኩ ጌታ ድንገት ትመጣለህ
ርሃቤን ጥማቴን ያኔ ታረካለህ
የጠበኩ ጌታ ድንገት ትመጣለህ
ርሃቤን ጥማቴን አንተው ታረካለህ

ኢየሱስ ኢየሱስ ወዳጄ
ኢየሱስ ኢየሱስመድሃኔቴ
ከአፌ አላወርድም ይህን ስምክን
አላርፍም አልረካም እስካገኝህ/2

Close